ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የተሰጠ ማስታወቂያ

News Item

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በዲግሪና በድህረ ምረቃ ትምህርት ስልጠና የሚሰጡ የመንግሥት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጡትን ትምህርትና ስልጠና ደረጃውን ጠብቀው እንዲሰጡ፣ ተማሪዎችም እውቅና እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት በተሰጣቸው ተቋማትና የስልጠና መስኮች እንዲማሩ እና ሰልጥነው ሲወጡ በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ኤጀንሲው ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ያገኙትን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትንና ፈቃድ ያገኙባቸውን ካምፓሶች እና የስልጠና መስኮች ዝርዝር እንዲሁም በድንገተኛ ኦዲት የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ በየጊዜው ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል። በዚሁ መሰረት በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ የሚከተለው መግለጫ ቀርቧል።

Back to the list